Detecting...

Please whitelist dirzon to continue.

or subscribe for ad-free contenct.

dirzon
  • Convert to Pdf
  • Reading List
  • Summary
  • Audiobook
  • Search
  • Upload
  • myzon
  • Log in
  • Register
English  አማርኛ  Français  العربية  Portuguese
Book of the day

አዋጅ ቁጥር 25_1984.pdf


Advertisement
  • word cloud

አዋጅ ቁጥር 25_1984.pdf
  • Extraction Summary

ትርጓሜ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጓሜ የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ አንቀጽ በተመለከተው የመብትና ግዴታ ምደባ መሠረት በመከፋፈሉ ወደሚፈጠሩት አዲስ ድርጅቶች ይዛወራል። በሌላ ሕግ የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ሥራ ድርጅት መከፋፈልን በሚመለከት በዚህ ንዑስ አንቀጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የነበረው አካል ነው። የድርጅቱ ጠቅላላ ንብረት ዕዳውን ለመክፈል በቂ በማይሆንበት ጊዜና የተፈቀደው ካፒታል በሙሉ ሳይከፈል ከቀረ ሂሣብ አጣሪዎች ቀሪው ሂሳብ እንዲከፈል ተቆጣጣሪውን ባለሥልጣን ይጠይቃሉ። ባልተጠናቀቁ የድርጅቱ ሥራዎች መነሻነት የሚቀርቡ የገንዘብ ጥያቄዎችን ለመሸፈን የሚያስፈልገው ገንዘብ ክርክሩ እስከሚወሰን ድረስ ለብቻ ተቀማጭ ሆኖ ይያዛል። ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ዘንድ ተቀምጠው ለገዐ ዓመት ይቆያሉ።

  • Cosine Similarity

ትርጓሜ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጓሜ የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ሙርጅት ማለት በመንግሥት ሙሉ ባለቤትነት የማምረት የማከፋፈል አገልግሎት የመስጠት ወይም ሌሎች የኢኮኖሚ ተግባሮችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በንግድ መልክ ለማካሄድ በዚህ አዋጅ መሠረት የተቋቋመ የመንግሥት ድርጅት ነው ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ማለት የመንግሥት የባቤትነት መብትን ለማስከበር ሲባል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚሰይመው አካል ነው ጠቅላላ ንብረት ማለት የድርጅት የማይንቀሳቀስና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ድርጅቱ ገና ያልተቀበላቸው ገቢዎች ጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳብ ሲሆን ግዙፍ ያልሆኑ ንብረቶች በቅድሚያ የተከፈሉ ወጪዎችንና ሌሎች ገቢ መሆን ያለባቸው ሂሳቦችን ይጨምራል የተጣራ ጠቅላላ ንብረት ማለት ከጠቅላላ ንብረት ላይ በተያዘው የሂሳብ ዓመት ውስጥ የሚከፈሉ ዕዳዎች በረጅም ጊዜ የሚከፈሉ ዕዳወች በቅድሚያ የተከፈለ ገቢና ሌሎች ዕዳዎች ተቀንሰው የሚቀረው ንብረት ነው ፒታል ማለት አንድ ድርጅት በተቋቋመ ጊዜና ከዚያም በኋላ መንግሥት የሚመደብለት የተጣራ ጠቅላላ ንብረት በተመደበበት ጊዜ ያለው ዋጋ ነው ዲተር ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ በተመለከተው መሠረት የማናቸውንም ድርጅት ሂሳብ የሚመረምር የተፈጥሮ ሰው ወይም የሕግ ሰውነት የተሰጠው አካል ነው የተጣራ ትርፍ ማለት ከገቢዎችና ከሌሎች ክፍያዎች ከተገኘው ገንዘብ ላይ ወጪዎችና በሂሳብ ዓመቱ ውስጥ ለሥራ ማስኬጃና ደመወዝ ባግባቡ ወጪ የተደረጉ ሂሳቦች የእርጅና ቅናሽዲፕሪቬሽን ወለድና ልዩ ልዩ ታክሶች ተቀንሰው የሚቀረው ሂሳብ ነው መንግሥት ማለት ማዕከላዊ መንግሥት ነው የመንግሥት የትርፍ ድርሻ ማለት ከተጣራው ትርፍ ላይ ወደ ሕጋዊ መጠባበቂያ ሂሳብና ሌሎች መጠባበቂያ ሂሳቦች ገቢ የሚሆነው ገንዘብ ተቀንሶ የሚቀረው ሂሳብ ነው ጥጦርድ ማለት በዚህ ዓዋጅ አንቀጽ እና አንቀጽ ገ መሠረት የሚቋቋም የድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ነው። አዲስ ክፍል የድርጅቱ አቋምና አመራር አቋም እያንዳንዱ ድርጅት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የሥራ አመራር ቦርድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል የተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ሥልጣንና ተግባር ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የዚህ አዋጅ አንቀጽ እንደተጠበቀ ሆኖ የቦርድ አባላትን ይመድባል ያነሳል ከሚመድባቸው አባላት መካከል የቦርዱን ሊቀመንበር ይሾማል ለቦርዱ አባላት ሊከፈል የሚገባውን አበል ይወስናል የውጭ ኦዲተሮችን ይሰይማል የድርጅቱን መነሻ ካፒታል ከመንግሥት ያስመድባል በዚህ አዋጅ አንቀጽ እና መሠረት የድርጅቱ ካፒታል እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ ይወስናል የድርጅቱ የተፈቀደ ካፒታል በአንቀጽ ዐኃ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ እንዲያልቅ የመጠባበቂያ ሂሳቦች እንዲያዙ ወይም ከመንግሥት ገንዘብ እንዲመደብ ያደርጋል ከቦርዱ በሚቀርብለት ሃሳብ መሠረት ከተጣራው ትርፍ ውስጥ በየዓመቱ ለመንግሥት ፈሰስ ሊደረግ የሚገባውን መጠን ይወስናል የድርጅቱን የሂሳብ ሪፖርትና የውጭ ኦዲት ሪፖርት ያጸድቃል በቦርዱ የሚቀርብለትን የድርጅቱን የኢንቨስትመንት ዕቅድ ያጸድቃል አስፈላጊ ሲሆን በቁጥጥሩ ሥር የሚገኝ ድርጅት እንዲፈርስ ከሌላ ድርጅት ጋር እንዲዋሐድ ወይም እንዲከፋፈል ወይም እንዲሸጥ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሃሳብ እያቀረበ ያስወስናል ከቦርዱ ጋር በመመካከር የድርጅቱን ዓመታዊና አጠቃላይ ግቦችን ያጸድቃል አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል ለቦርዱ የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር እንደጠበቀ ሆኖ የመንግሥት የባለቤትነት መብትን ለማስከበር የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል። የድርጅቱን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይቀጥራል ደመወዝና አበሉን ይወስናል ያሰናብታል ለድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑ የሥራ ኃላፊዎችን ቅጥር ምደባና ስንብት ደመወዝና አበል ያጸድቃል የድርጅቱን የሥራ ፕሮግራም በጀትና የውስጥ ደንብ ያጸድቃል አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል የድርጅቱን የረጅም ጊዜ ብድሮችና ክሬዲቶች ያጸድቃል በድርጅቱ ሕልውና ላይ ወሳኝነት የሌላቸውን ቋሚ ንብረቶች ሽያጭ ያጸድቃል የድርጅቱ ሂሣቦችና ንብረቶች ባግባቡ መያዛቸውን ያረጋግጣል ለድርጅቱ ኦዲተሮች የድርጅቱን የሂሳብ መዝገቦች ለተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ደግሞ ስለድርጅቱ የሥራ አፈጻጸም ወቅታዊ ሪፖርትና የሂሳብ መግለጫዎች ያቀርባል የድርጅቱ ካፒታል እንዲጨምር ወይም እንዲቀንስ ለተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ሐሳብ ያቀርባል የቦርድ አባላት ተጠያቂነት የቦርድ አባላት በዚህ አዋጅ መሠረት የተሰጣቸውን ተግባር በጥንቃቄ መፈጸም አለባቸው። ክፍል የድርጅቱ ካፒታል ድርጅት ለማቋቋም ስለሚያስፈልገው ካፒታል ማናቸውም ድርጅት ካፒታል ይኖረዋል አንድ ድርጅት ለማቋቋም የሚያስፈልገውን መነሻ ካፒታል ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን በመንግሥት እንዲመደብለት ያደርጋል። ካፒታል ስለመቀነስ የሦስተኛ ወገኖች መብት ሳይነካ የአንድ ድርጅት ካፒታል የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ሊቀንስ ይችላል የድርጅቱ ካፒታል እንዲቀነስ ኦዲተሮች ሐሳብ ሲያቀርቡ በድርጅቱ ቦርድ በሚቀርበው ሐሳብ መሠረት ካፒታሉ እንዲቀነስ ሲወሰን የድርጅቱ የተፈቀደ ካፒታል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ዐ ንዑስ አንቀጽ መሠረት በሙሉ ተከፍሎ ያላለቀ ሲሆን። የስም አጠቃቀም ሁኔታዎች የአንድ ድርጅት ስም አመራረጥ በዚህ አዋጅ አንቀጽ በተመለከተው መሠረት መሆኑን ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ያረጋግጣል። የሂሳብ ዓመት ሂሣብ መዝጋትና ዓመታዊ ሪፖርት የአንድ ድርጅት የሂሳብ ዓመት በተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ይወሰናል ማናቸውም ድርጅት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ሂሣቡን ይዘጋል። የሚከፋፈል ድርጅት መብትና ግዴታ በዚህ አዋጅ አንቀጽ በተመለከተው የመብትና ግዴታ ምደባ መሠረት በመከፋፈሉ ወደሚፈጠሩት አዲስ ድርጅቶች ይዛወራል። በሌላ ሕግ የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ሥራ ድርጅት መከፋፈልን በሚመለከት በዚህ ንዑስ አንቀጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ማለት በዚያው ሕግ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የነበረው አካል ነው። ክፍል ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች በሌሎች ሕጐች ስለተቋቋሙ ድርጅቶች ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በሌላ ሕግ የተቋቋመ ማንኛውም ድርጅት በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጣ ደንብ እንደገና እንዲቋቋም ተከፋፍሎ አዲስ በሚቋቋሙ ድርጅቶች እንዲተካ ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር እንዲዋሃድ ሊደረግ ወይም በዚህ አዋጅ መሠረት እንደተቋቋመ ተቆጥሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ሊሰይምለትና በዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች መሠረት እንዲተዳደር ሊደረግ ይችላል። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ገሀ መሠረት የሚቋቋሙ ድርጅቶች አንድን ድርጅት በመከፋፈል ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ድርጅቶችን በማዋሐድ የሚፈጠሩ ሲሆን የተከፈለውን ድርጅት ወይም የተዋሐዱትን ድርጅቶች ሂሳብ መዝጋትና መመርመር እንዲሁም መብትና ግዴታ ማስተላለፍን በሚመለከት የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፖ እና ፀ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዚህ አዋጅ መሠረት ድርጅት የማቋቋም ለሚያቋቁመው ድርጅት ካፒታል የመመደብና ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የመሰየም ድርጅት የማፍረስ አንድ ድርጅት ከሌላ ድርጅት ጋር እንዲዋሐድ ወይም እንዲከፋፈል የመወሰን የሶስተኛ ወገኖች መብት ሳይነካ ማናቸውም ድርጅት በንግድ ሕግ መሠረት የንግድ ማኅበር ሆኖ እንዲቋቋም ማናቸውም ድርጅት እንዲሸጥ ወይም በሌላ አኳኋን ድርጅቱ ወይም ማኔጅመንቱ እንዲተላለፍ የመወሰን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ሀ መሠረት በሚቋቋም የንግድ ማኅበር በመንግሥት የተያዘ አክስዮን እንዲሸጥ የመወሰን ይህን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ደንቦችን የማውጣት ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል።

  • N.B. This Summary is Very Experimental!! based on the following scripts from:
    • https://github.com/millzon/textSummarizer-am
    • https://github.com/icoxfog417/awesome-text-summarization#motivation
Download Searchable PDF Download PDF

Advertisement
Bottom banner

Download options | Convert to Pdf | Reading List | Advertise on dirzon

© dirzon | Terms of Service | Privacy | About | Services | Contact